TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Dessie

" የህክምና ቁሳቁሶቹን ባለሞያዎች መጥተው ነው የፈቷቸው " - የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

በአማራ ክልል እጅግ ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው ሆስፒታሎች መካከል የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዋነኝነት ይጠቀሳል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ ሆስፒታሉ 80 ዓመቱ ሲሆን የደረሰበት ጉዳት 80 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ከ0 እንዲጀምር እንደሚያደርገው ነው የምንቆጥረው ብለዋል።

ሆስፒታሉ በህወሓት ኃይሎች የመድሃኒት ቤቱ አንድም ሳይተርፍ ተዘርፏል/ወድሟል፣ የላብራቶሪ እቃዎች ተዘርፈዋል፣ በምስራቅ አማራ ብቸኛው የኦክሲጅን ማምረቻው ተዘርፎ ተወስዷል የተረፈው አገልግሎት እንዳይሰጥ ተደርጎ ወድሟል፤ በምስራቅ አማራ ብቸኛው የካንሰር ህክምና መስጫ ቁሳቁሶች ተዘርፎ ተወስዷል።

ዶ/ር ሃይማኖት አየለ ዝርፊያው በተጠና መልኩ እንደተካሄደና ባለሞያዎች መጥተው እንደፈቷቸው አሳውቀዋል።

ሆስፒታሉ አሁን ላይ በተወሰነ መልኩ ወደአገልግሎት የተመለሰ ሲሆን የወሊድ፣ ድንገተኛ አገልግሎት እና የተመላላሽ ታካሚዎችን እያስተናገደ ሲሆን ሆስፒታሉ ታካሚዎችን እያስተናገደ ያለው ቁሳቁስ ስላለው ሳይሆን ባለሞያዎች ባላቸው ሞያ ብቻ አገልግሎት መስጠት ስላለባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ዶ/ር ሃይማኖት ገለፃ በሆስፒታሉ በወር በአማካይ 800 እናቶች በሆስፒታሉ ሲወልዱ እንደነበር አስታውሰው አገልግሎት በመቋረጡ በርካቶች ለጉዳት መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአማራ ክልል ምስራቅ አማራ፣ አፋር ክልል እንዲሁም የትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በአጠቃላይ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይገለገሉበት እንደነበር የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ለሬድዮ ጣብያው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#MoH

የጤና ተቋማት ወደነበሩበት ለመመለስ ርብርብር እየተደረገ ነው።

በግጭት ምክንያት የወደሙና የተጎዱ ጤና ተቋማትን ወደነበሩበት ለመመለስ እና የጤና አገልግሎት ለማስጀመር የአዲስ አበባ ጤና ቢሮና የፌዴራል ሆስፒታሎችን ከወደሙ ሆስፒታሎች ጋር በማስተሳሰር ድጋፍ እንዲያደርጉ ሰፊ ስራ መጀመሩን ከጤና ሚኒስቴር ተሰምቷል።

በቀጣይ ሌሎች ክልሎች እና ዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎችን በማስተባበር የድጋፍ ስራው በስፋት እንዲቀጥል ይደረጋል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት:-

• ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌንየም ሜዲካል ኮሌጅ 👉 ደሴ ሆስፒታልን፤
• ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 👉 ከልዋን ሆስፒታልና ቦሩ ሜዳ ሆስፒታልን፤
• አቤት ሆስፒታል 👉 ባቲ ሆስፒታልን፤
• የካቲት 12 ሆስፒታል 👉 ወረ ኢሉ ሆስፒታን፤
• ምኒሊክ ሆስፒታል 👉 መሃል ሜዳ ሆስፒታልን፤
• ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል 👉 ከሚሴ ሆስፒታልን፤
• ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል 👉 ሀይቅ ሆስፒታልን፤
• ራስ ደስታ ሆስፒታል 👉 ደብረ ሲና ሆስፒታልን፤
• አለርት ሆስፒታል 👉 ኮምቦልቻ ሆስፒታልን፤
• ዘውዲቱ ሆስፒታል 👉 ደጎሎ ሆስፒታልን፤
• ጋንዲ ሆስፒታል 👉 ሞላሌ ሆስፒታልን፤
• አማኑኤል ሆስፒታል የአእምሮ ጤናና የስነልቦና ማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ 👉 ለሁሉም ሆስፒታሎች ድጋፍ ለመስጠት ትስስር በመፍጠር ወደ ስራ ገብተዋል።

ጤና ሚኒስቴር የአዲስ አበባ እና ፌዴራል ሆስፒታሎች እያደረጉ ስላሉት ርብርብ ምስጋና አቅርቧል።

ሆስፒታሎቹ በአፋጣኝ ስራ ለማስጀመር ከክልሉ እና ከጤና ሚንስቴር ጋር እየሰሩ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ወደነበሩበት ለመመለስ አሁንም ከፍተኛ መዋለ ነዋይና ድጋፍ ስለሚያስፈልግ ሁሉም የሚመለከተው አካል ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
" ለ11 ቀናት መሳቅ አይቻልም ፤ ወደ መጠጥ ቤት መሄድ እና መጠጥ መጠጣትም አይቻልም " - ሰሜን ኮሪያ

የቀድሞውን የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኢልን 10ኛ የሙት ዓመት በማስመልከት በሀገሪቱ ለ11 ቀናት መሳቅ ተከለከለ፡፡

ኪም ጆንግ ኢል ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በአውሮፓውያኑ 2011 ሲሆን ዘንድሮ 10 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡

የቀድሞውን መሪ 10ኛ የሙት ዓመት አስመልክቶም በሀገሪቱ መሳቅና መጠጥ መጠጣት መከልከሉን ዴይሊ ሜል ዘግቧል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ሰሜን ኮሪያውያን ወደ ግሮሰሪ መሄድ እንደማይችሉ የተነገራቸውም ሲሆን በመታሰቢያ የዚህ የሀዘን ቀናቱ ውስጥ ቤተሰቡ የሞተበት ሰው ጮክ ብሎ ማልቀስ እንደማይችል ሰሜን ኮሪያ አስጠንቅቃለች፡፡

የልደት በዓላቸው በ11ዱ የሀዘን ቀናት ውስጥ የሆነባቸው ግለሰቦች ይህንን ማድረግ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።

ዛሬ አርብ ከደቂቃዎች በፊት በፒዮንግያንግ የነበረው የቢዝነስና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ለ5 ያል ደቂቃዎች ቆሞ የኢል 10ኛ ሙት ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በ69 ዓመታቸው በፈረንጆቹ ታህሳስ 17 ቀን 2011 በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የሰሜን ኮሪያ መሪ ሀገራቸውን ለ17 ዓመታት መርተዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ / ዴይሊ ሜይል

@tikvahethiopia
#TechZone

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!              
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599  ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
" የሚመጡ እንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ተጠናቋል " - ፌዴራል ፖሊስ

በ "አንድ ሚሊዮን ዳያስፖራ ወደ ሀገር ቤት " ጥሪ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ እንግዶችንን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ፌዴራል ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ ሆነ በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት አስቀድሞ ማድረጉን ገልጿል።

የጸጥታና ደህንነት ተግባሩን የኮማንድ ፖስቱ የጸጥታ መዋቅር ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የሚያከናውን ሲሆን ጥምር የጸጥታ ሃይሎች አስቀድሞ የጸጥታ ስጋት የሆኑ ነገሮችን በመለየት እንግዶቹ በሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ምንም አይነት ችግር እንዳይገጥማቸው በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ፖሊስ አሳውቋል።

እንግዶቹ ለሚያጋጥማቸው ማንኛውንም ነገር መረጃ ለመስጠትና አስቀድሞ መረጃ ለማግኘት የሚችሉባቸውን አድራሻዎች ከፌደራል ፖሊስና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ማህበራዊ ገጾች ማግኘት ይችላሉ።

እንግዶች በስፋት ወደ ሀገር ሲገቡ ደግሞ አድራሻዎቹን የማሳወቅ ስራ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Update

ሀይቅ፣ ቢስቲማና ለሚ ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
Turkey 🤝 Africa

የቱርኩ ፕሬዜዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እና የሱማሊያው ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብድላሂ ፈርማጆ ወይይት አካሄዱ።

3ኛው የቱርክ-አፍሪካ ትብብር ጉባኤ በኢስታንቡል እየተካሄደ ይገኛል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን የቱርክ እና የሱማሊያ መሪዎች ተገነኝተው ውይይት እንዳደረጉ ተሰምቷል፤ የውይይቱን ይዘት በተመለከተ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
#Update

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ከፕሬዜዳንት ኤርዶጋን ጋር ተወያዩ።

ከቱርክና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የልዑካን ቡድናቸው ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ዛሬ አካሂደዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፥ " የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ሁሌም በመከባበር ላይ የተመሠረተ ነው። ትብብራችን በገንቢ ተሳትፎ ላይ በመመሥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ልዩ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ስብሰባውን በቀጥታ ለመከታተል ይህን ይጫኑ : https://media.un.org/en/asset/k11/k119r483hu @tikvahethiopia
#UN_Human_Rights_Council

ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ጸድቋል።

በአውሮፓ ህብረት ጠያቂነት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ዛሬ በተካሄደው ልዩ ስብሰባ ነው የፀደቀው።

የውሳኔ ሃሳቡ በ21 ድጋፍ እና በ15 ተቃውሞ የጸደቀ ሲሆን 11 ሃገራት ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል።

ለተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምን ይዟል ?

በአውሮፓ ህብረት አማካኝነት ቀርቦ የፀደቀው የውሳኔ ሀሳብ በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምር ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች ቡድን በኢትዮጵያ እንዲሰማራ የሚጠይቅ ነው።

የውሳኔ ሀሳቡ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጋር በጥምረት ያደረጉት ምርመራ ውጤት መነሻ አድርጎ ተጨማሪ ምርመራ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን እንዲሰማራ የሚጠይቅ ነው።

ዓለም አቀፍ መርማሪ ቡድኑ በኢትዮጵያ የአንድ ዓመት ቆይታ እንዲኖረው የሚጠይቅ ሲሆን የሚላከው ቡድን ከሚያደርገው ምርመራ በተጨማሪ ፦
- የሽግግር ፍትህ ተግባራዊ የሚያደርግበትን፣
- ዕርቅና ተጠያቂነት የሚሰፍንበት
- ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸው ማገገም እንዲችሉ ምክረ ሃሳብና የቴክኒክ ድጋፍ የመስጠት ኃላፊነት እንዲኖረው ይጠይቃል።

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት #መርሳ እና #ግራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋቃ።

የአትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በቆቦ ግንባር ቀደም ብሎ የዞብል ከፍተኛ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን፣ በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን ጨምሮ ተቆጣጥሯል፡፡

በዞብል ደቡብ አቅጣጫ ደግሞ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የነበረው የወገን ጦር አሁን ደግሞ የጉራ ወርቄ ከፍተኛ ሰንሰለታማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ በማጽዳት፣ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን የወልድያ መቀሌ መሥመር አሰፋፍቶ፣ ወደ ወልድያ በቅርብ ርቀት እየገሠገሠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ባለፈው ውጫሌ ከተማን ነጸ ያወጣው የወገን ጦር፣ በዚሁ ግንባር የውጫሌ ወረዳን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የውርጌሳ፣ የሊብሶ፣የግራና፣ የመርሳ፣ የኪሌ፣ከተሞችንና በሰሜን ወሎ የሐርቡ ወረዳን ከፍተኛ ሰንሰለታማ ተራሮችን በእጁ አስገብቷል።

በእነዚህ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ጀግኖቹ የወገን ጥምር ጦር በንሥሮቹ አየር ኃይላችን በመታገዝ ጠላትን ከመርሳ በስተጀርባ ቆርጦ በመግባት፣ በውጫሌና ውርጌሳ መካከል የነበረውን ጠላት ሙለሉ በሙሉ ደምስሰውታል፤ ምርኮኛና ቁስለኛም አድርገውታል ብሏል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፥ የአካባቢ ኅብረተሰብ ከወገን ጥምር ጦር ጋር በመቀናጀት፣ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚሸሸውን ጠላት ከየጢሻው እየመነጠረ በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈጽሟል ብሏል።

አክሎም " ጠላት የዘረፈውን ንብረትና ተተኳሾቹን ፈጽሞ ይዞ እንዳይወጣ አድርጎታል፡፡ የወገን ጥምር ጦር በወልድያና ሐራ ከተሞች መካከል የሚገኘውንና መውጫ ያጣውን ጠላት ለመደምሰስ፣ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው " ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia