TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

በአፋር ክልል ለ #ኦፕቲካል_ፋይበር_ጥገና ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ኃይል ይቋረጣል።

የኮምቦልቻ - ሠመራ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ትናንት ተጠናቋል።

ነገግ ግን የኦፕቲካል ፋይበር ጥገና ባለመጠናቀቁ በአፋር ክልል ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ኃይል እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

ኃይል ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች ትናንት የተጠናቀቁ ቢሆንም የኦፕቲካል ፋይበር ጥገና ቀሪ ስራዎችን ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በመስራት ሙሉ በሙሉ ጥገናውን ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የኦፕቲካል ፋይበር ጥገናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለግማሽ ቀን የሚካሄድ ይሆናል።

ሥራዎቹ እንደተጠናቀቁ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመነጋገር የአፋር ከተሞች ኃይል የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።

@tikvahethiopia
“ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባት አስደሳች ነው " - ዲያን ካስተሊክ

የሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም፣ ቮዳፎን፣ ሱሚቶሞ እና ሲዲሲ ጥምረት ልዑካንና የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አመራሮቻችን ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ኢንጂነር ባልቻ ጋር ተወያይተዋል።

ከጥምረቱ አባላት አንዱ የሆነው የቮዳኮም ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲያን ካስተሊክ፣ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ እስካሁን ላደረገው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና መልካም ግንኙነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሚስተር ዲያን ፥ “ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባት አስደሳች ነው፡፡ እንደ ቮዳኮም ሌሎች አገራት ያለንን ልምድ ማካፈል መቻላችንም ያስደስተናል፡፡ ቮዳኮም ለዲጂታል አካታችነት እና ለፋይናንስ አገልግሎቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ በኢትዮጵያ ከቴሌኮም አቅርቦት በተጨማሪ ሌሎች እገዛዎችን ለማድረግ እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

ኢ/ር ባልቻ ሬባ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ወደ አገር ውስጥ ለሥራ የሚያስፈልጉትን ቁሳቁስ በማስገባትና የባለድርሻ አካላት ግንኙነትን በማመቻቸት ሳፋሪኮም ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ማቅረብ እንዲችል እገዛ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

የሳፋሪኮም የውጪ ጉዳዮች እና ሬጉላቶሪ ኃላፊ ማቲው ሃርቬ-ሃሪሰን፣ ድርጅታችን የፈቃድ ግዴታዎችን እና መመሪያዎችን በመከተል በተቻለው ፍጥነት የኔትዎርክ አቅርቦቱን ለማቀላጠፍ አፅንዖት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ሚስተር ማቲው የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በጉምሩክ እና ኢምፖርት ሂደቶች ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ውይይቱ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሚገኝበትን የዝግጅት ደረጃ እና በቀጣይ የሚሠሩ ሥራዎችን በመግለጽ ተጠናቋል፡፡

#ሳፋሪኮምኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
' 07 ' 👉 የስልክ ቁጥር መለያ - #SafaricomETH

ቢዝነስ ዴይሊ ጋዜጣ ፥ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚጀምረው የሞባይል ስልክ አገልግሎት የስልክ ቁጥሮች መለያ ቁጥር 07 እንደሚሆን ማስታወቁን ዘግቧል።

እንደጋዜጣው ዘገባ ሳፋሪኮም በኬንያ ለሚሰጠው የሞባይል አገልግሎት የሚጠቀመው መለያ ቁጥር 07 ሲሆን አሁን ኢትዮ ቴሌኮም ከሚጠቀምበት መለያ ቁጥር 09. ቀጥሎ በሀገሪቱ ሁለተኛው ይሆናል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን እየቀጠረ ሲሆን ጥር ወር ላይ ብቻ 100 ሠራተኞችን እንደሚቀጥር አሳውቋል።

ምንጭ፦ https://www.businessdailyafrica.com/bd/corporate/companies/safaricom-set-use-07-prefix-ethiopia-phones-3655590

@tikvahethiopia
#MarakiEngraving

🎄ዘመን ተሻጋሪ ጊዜ ማይሽረው ልዩ ስጦታ🎄
🎁ከእንጨት የተሠራ Postcard
☎️0953144144 / 0915089555
📌አድራሻ- መገናኛ ገነት ኮሜርሻል 4ኛ ፎቅ 412
👇join our channel
https://publielectoral.lat/maraki_engraving
#Fagta

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብል ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ።

በአዊ ብ/አስተዳደር በፋግታ ለኮማ ወረዳ በጋፈራ እና በዘበላ ግራይታ ቀበሌ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በመከር ሰብልና በመስኖ ሰብል ከባድ ጉዳት ማድረሱን ተጎጂ አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ጉዳት ከደረሰባቸው የመኸር ሰብሎች መካከል ጤፍ ፣ ስንዴ፣ አተር እና ገብስ እንዲሁም በመስኖ ድንች፣ የጓሮ አትክል ይገኙበታል።

የፋግታ ኮሙዩኒኬሽን ፥ የጉዳት መጠኑን በተመለከተ ተጣርቶ በቀጣይ እንደሚገልፅ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
' We Are The World '

በ1977 ዓ/ም በኢትዮጵያ ውስጥ ተከስቶ ለነበረው ድርቅ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ የተዘጋጀውን 'We Are The Wolrd' የተሰኘውን ህብረ ዝማሬ ካቀናበሩት፣ ከመሩት እና ለአድማጭ ካቀረቡት የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች አንዱ የነበሩት ኬን ክራገን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ፕሮድዩሰር፣ ስራ አስኪያጅ እና በጎ አድራጊው ክራገን በ85 ዓመታቸው በአሜሪካ ሎስ አጀለስ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንዳረፉ ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል።

ክራገን ከነ ሎዮኔል ሪቼ፣ ኬኒ ሮጀርስ ፣ ማይክል ጃክሰን እና ሎሎችም የዓለማችን አንጋፋ የጥበብ ሰዎች ጋር በመሆን የሰሩት ' We Are The World ' የተሰኘው ሙዚቃ በወቅቱ የዓመቱን ኤሚ አዋርድ አሸናፊ የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ ሰዓትም በ30,000 የሬድዮ ጣቢያዎች ላይ ተሰራጭቶ በመላው ዓለም ሚሊዮኖችን አነቃቅቷል።

ክራገን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ሜዳልያ ተሸላሚ ናቸው።

መረጃው የአሶሼት ፕሬስ ነው።

🎵እንድታስታውሱት ዘንድ ' We Are The world ' ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
" የአሜሪካ ጦር በስህተት በጣላቸው ቦንቦች ብቻ ከ1 ሺ 300 በላይ ንጹሃን ሰዎች ተገድለዋል " - ሰነድ

አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ባካሄደቻቸው የአየር ድብደባዎች ላይ የፈፀመችውን ስህተት የሚያሳይ ሰነድ ይፋ ሆኗል።

በቅርቡ ከአሜሪካው መከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጎን እንደወጣ የተነገረው ሰነድ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ባካሄደቻቸው የአየር ድብደባዎች በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የሚያመላክት ነው።

በስህተት ተፈጽመዋል በተባሉት የአየር ድብደባዎቹም ህይወታቸው ካለፈ ንጹሃን ዜጎች መካከል በርካታ ህጻናት እንደሚገኙበት ተመላክቷል።

በሰነድ ላይ መካከለኛው ምስራቅ የተፈፀሙ አብዛኞች የአየር ድብደባዎች ከወታደራዊ ደህንነት እውቀት ውጪ የተፈፀሙ ናቸው ተብሏል።

በቅርቡ የተሰበሰቡ ተዓማኒ ሰነዶች እንደሚያመላክቱት የአሜሪካ ጦር በስህተት በጣላቸው ቦንቦች ብቻ ከ1 ሺህ 300 በላይ ንጹሃን ሰዎች እንደተገደሉ ያመላክታል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ግልፀኝነትን ተጠያቂነትን ከማስፈር አንጻር እስካሁን በግልጽ የተሰራ ስራ አለመኖሩ / ለተፈፀሙ ስህተቶች አስካሁን ተጠያቂ የተደረገ አካል እንደሌለ ተገልጿል።

በሰነዱ ላይ የአሜሪካ ልዩ ኃይል እ.ኤ.አ. በሐምሌ ወር 2016 ላይ በሶሪያ የፈፀመው የአየር ድብደባ ለአብነት ተቀምጧል።

በዚህም የአሜሪካ ልዩ ኃይል በሶሪያ የአሸባሪው ISIS የተጠቀምበታል ተብሎ የታመነ ሶስት ስፍራዎች ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ከ120 በላይ አርሶ አደሮች እና የገጠራማ አካባ ነዋሪዎች መገደላቸው ተመላክቷል።

መረጃውን ኒው ዮርክ ታይምስ የተባለው የአሜሪካ ጋዜጣ ነው ይዞት የወጣው።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቀጠለው የሱዳን ታቃውሞ ...

ሱዳን ውስጥ አሁንም ተቃውሞ ቀጥሏል።

ዛሬ ካርቱም ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የጥቅምት 25ቱን (እኤአ) ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ወጥተው ነበር።

ሰልፉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰው ቁጥር የተሳተፈበት ሲሆን የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተሰምቷል።

ባለፈው ወር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ቢመለሱም ወደራዊ መፈንቅለ መንግስቱን በመቃወም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁን ድረስ ቀጥሏል፤ ተቃዋሚዎች በመንግስት ውስጥ ምንም አይነት ወታደራዊ ተሳትፎ እንዳይኖር እየጠየቁ ናቸው።

ዛሬ የቀድሞው መሪ ኦማር አልበሽር ከስልጣን እንዲወርዱ ምክንያት የሆነው ህዝባዊ እምቢተኝነት የተነሳበት ሶስተኛ አመት ምክንያት አድርገው ተቃዋሚዎች ወደ ፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት አቅንተዋል።

ሰልፈኞቹ ከቤተ መንግስቱ አንድ ኪሎ ሜትር በማይሆን ርቀት ላይ ተሰብስበው " ህዝቡ ጠንካራ ነው ፤ ማፈግፈግ የማይታሰብ ነው " እያሉ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ነበር ፤ በኃላም የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ሰልፉን ለመበተን የጣሩ ሲሆን ሰልፈኞች ጎዳናዎች ላይ ሲሯሯጡ ታይተዋል።

የጸጥታ ሃይሎች ከሰልፉ ቀደም ብሎ በመዲናይቱ ዋና ዋና መንገዶችንና ድልድዮችን ሲዘጉ ነበር።

በሌሎችም የሀገሪቱ ከተሞችም የተቃውሞ ሰልፎች ታቅዶ እንደነበር የተሰማ ሲሆን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጩ ምስሎች በቀይ ባህር ዳርቻ ፖርት ሱዳን እና በዳርፉር ምዕራባዊ ክልል ኤል-ዴዪን ህዝባዊ ተቃውሞ እንደነበረ ሲያሳዩ ነበር።

@tikvahethiopia
" ከህወሃት ጋር ምንም አይነት ግንኙነትም፣ ንግግርም፣ ድርድርም አንፈልግም "- አቶ ሙሳ አደም

የአፋር ህዝብ ፓርቲ ከህወሃት ጋር ምንም አይነት ንግግርና ድርድር ማድረግ እንደማይፈልግ አስታወቀ።

የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ሙሳ አደም ለአል ዐይን በሰጡት ቃል፤ አሁን ላይ በሕዝብ ላይ ትንኮሳና ጥቃት እያደረሰ ካለው የህወሃት ቡድን ጋር እንደ ፓርቲ መነጋገርም ሆነ መደራደር እንደማይፈልጉ ገልፀዋል።

አቶ ሙሳ ህወሃት ትናንትና ከሰዓት በኋላ በሰሜን አፋር በኩል አዲስ ጥቃት መክፈቱን ተናግረዋል።

ህወሓት በመጀመሪያ በአፋር ክልል በራህሌ ጥቃት ሰንዝሮ እንደነበር አስታውሰዋል።

አቶ ሙሳ፥ ህወሃት የአብአላ ከተማን ለመቆጣጠር 3 እና 4 ጊዜ ሙከራ ማድረጉን ገልጸው በአካባቢው ያለው የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት ይህንን ጥቃት እየመከተ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአፋር ሕዝብ ፓርቲ ከስር መሰረቱ የተቋቋመው ህወሃት በሕዝብ ላይ ሲፈጽመው የነበረውን የረጅም ዘመናት ግፍና መከራን ለመታገል ነው ያሉት አቶ ሙሳ ፓርቲያቸው ከሕወሃት ጋር ምንም አይነት ግንኑነትም፣ ንግግርም፣ድርድርም እንደማይፈልግ ተናግረዋል።

አቶ ሙሳ፤ እንደፓርቲ ከህወሃት ጋር ድሮም ምንም ንግግር አልነበረንም ያሉ ሲሆን፤ ወደፊትም ንግግር ሊኖር አይችልም ሲሉ ገልጸዋል።

ሊቀመንበሩ፥ “ህወሃት የአፋርን ሕዝብ ብዙ መከራ አብልቷል” ያሉ ሲሆን የፓርቲውን አመራሮች አሸባሪ ብሎ ፈርጆ እንደነበር አስታውሰዋል።

እንደፓርቲ ከህወሃት ጋር መነጋገር እንደማይፈልጉ የተናገሩት አቶ ሙሳ እንደሀገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተነጋግሮ ችግሮቹን በጠረንጴዛ ዙሪያ መፍታት ከቻለ “እኛም እንደ አንድ የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም የምናገኝበት አጋጣሚ ሊኖር ስለሚችል የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚወስነውን አብረን የምንወስን ይሆናል” ብለዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
#HongKong

በሆንግ ኮንግ በተደረገ የሕግ አውጪ ምክር ቤት ምርጫ የማዕከላዊ ቻይና መንግሥት ደጋፊ የሆኑ ዕጩዎች በከፍተኛ ድምጽ ማሸነፋቸው ተሰምቷል።

ቻይና በግዛቲቱ ያወጣችው የደኅንነት ሕግ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ እና የሆንግ ኮንግ የምርጫ ሕግን ከቀየረች በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው የሕግ አውጪው ምክር ቤት ምርጫ ነው።

የምርጫ ሕጉ ቤይጂንግ የእያንዳንዱን ዕጩ የጀርባ ታሪክ እንድትመረምር መብት የሚሰጥ ነው።

የግዛቲቱ ኃላፊዎች መረጋጋትን ለማምጣት ሲባል ምርጫው አስፈላጊ ነው ቢሉም ተቺዎች ግን ዴሞክራሲን ያዳከመ ሲሉ ገልጸውታል።

ኃላፊዎቹ እንዳሉት እድሜው ለመምረጥ ከደረሰው የግዛቲቷ ነዋሪ ውስጥ 30‌ በመቶ የሚሆነው ብቻ ድምጹን ሰጥቷል።

በተለምዶ ሌግኮ ወይም የሆንግ ኮንግ ትንሹ ፓርላማ ተብሎ የሚጠራው ይህ የሕግ አውጪ ምክር ቤት ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ሲሆን በከተማዋ ሕግ ማውጣት እና ማሻሻልን ጨምሮ የተለያዩ ሥልጣኖች አሉት።

ምክር ቤቱ ካሉት አጠቃላይ 90 ወንበሮች ውስጥ 20ዎቹ ብቻ በሕዝብ ሲመረጡ 40ዎቹ በቤይጂንግ የምርጫ ኮሚቴ እንዲሁም ቀሪው 30 ደግሞ የልዩ ጥቅም ቡድን በሚባሉት እና በንግዱ ዓለም ውስጥ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቡድኖች የሚመርጡት ነው።

በታሪክ እነዚህ የንግድ ማኅበራት ወደቤይጂንግ እንደሚያደሉ ይታወቃል ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
10 ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ተመረቁ።

ባሳለፍነው ሳምንት ኦርቢት የኢኖቬሽን ማጎልበቻ ማዕከል (OIH) ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን 10 አዳዲስ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችን አስመርቋል።

የተመረቁት ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶቹ በጤና፣ በትምህርትና አገልግሎት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን የቴክኖሎጂ መፍትሄ መስጠት ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው።

ኦርቢት የኢኖቬሽን ማጎልበቻ ማዕከል አዳዲስ ጀማሪ ድርጅቶችን ሲያስመርቅ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደም 5 ድርጅቶችን አስመርቋል።

እንዴት ነው ድርጅቶቹ የሚመረጡት ?

- ለአንድ ወር በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ዘመቻ ይካሄዳል ፤ ጥሪ ይቀርባል።
- ጥሪውን ተከትሎ የሚያመለክቱ ጀማሪ ድርጅቶች ይጠራሉ።
- የተወሰነ ቁጥር ተመርጠው የሶስት ቀን ስልጠና ይሰጣቸዋል።
- ከስልጠናው በኃላ በሚያቀርቡት ፕረዘንቴሽን እንዲሁም አዋጭነታቸው እና ችግርን የማፍታት አቅማቸው ተገግምግሞ የተመረጡ ወደ 4 ወር ስልጠና ይገባሉ።
- የ4 ወሩ ስልጠና ብራንዲንግ፣ ማርኬቲንግ ስትራቴጂ ፣ ቢዝነስ ስትራቴጂ ... ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ጥልቅ እውቀት እንዲያገኙ ይደረጋል።
- ከስጠናው በኃላ ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣቸዋል።
- በመጨረሻም የኢንቬስተሮች ጋር የሚገናኙበት መድረክ ይመቻችላቸዋል።

እስካሁን 15 ጀማሪ ድርጅት ከአዲስ አበባ የወጡ ሲሆን በቀጣይ ስራውን በስፋት ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ እንደ ጎንደር፣ ባህርዳር ፣አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ደሴ በመሳሰሉ ከተሞች ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ኦርቢት የኢኖቬሽን አሳውቆናል።

* ባለፈው ሳምንት ስለተመረቁት ጀማሪ ድርጅቶች ዝርዝር መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia