TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አደይ

ዘወትር ከሰኞ-አርብ ማታ በ2:00 ሰዓት በድጋሚ ከረፋዱ 4:30 እና ከሰዓት በ9:30 እንዲሁም እሁድ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ የሳምንቱ አምስት ተከታታይ ክፍሎች በአቦል ቻናል (146) ይቀርባሉ።

ክፍያ ለመፈፀም፣ፓኬጅዎን ለመቀየር እንዲሁም ለሌሎች የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን
የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ : https://bit.ly/2WDuBLk

የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ : https://bit.ly/3D2O1t4

#DStvEthiopia #DStvየራሳችን #DStvSelfService
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

"ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም" በሚል መሪቃል ነገ ታህሳስ 10 ቀን 2014 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ ሰልፍ ይካሄዳል፡፡

ሰልፉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበበ ፖሊስ አስታውቋል።

ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

የሚዘጉ መንገዶች (ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ) ፦

• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ እና ታች መንገዶች

• ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ ላይ እና ታች መንገዶች

• ከ4 ኪሎ በውጪ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሄራዊ- ቤተ መንግስት

• ከአዋሬ ካዛንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ መብራት

• ከሜክሲኮ ፣ ለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ
የሚወስደው መንገድ ለገሃር ትራፊክ መብራት ላይ

• ከሰንጋ ተራ ብሄራዊ ቴአትር ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት

• በቸርችል ጎዳና ፖስታ ቤት፣ ሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ መብራት

• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ እና ለቀላል ተሸከርካሪ ጥላሁን አደባባይ ዝግ ይሆናል።

ከዚህ በተጨማሪም ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ዙሪያ እና በእነዚህ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update Turkey 🤝 Africa የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በቱርክ አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፦ - ወደ 19ኛው ክፍለ ዘመን ስንመለስ ከአፍሪካ ጋር ጥልቅ ግንኙነት አለን። - አፍሪካን ለመደገፍ ቁርጠኞች ነን። - ትብብራችን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ እንጂ ኢምፔሪያሊዝም ወይም ኦሬንታሊዝም አይደለም።…
Turkey 🤝 Africa

በቱርክ ፣ ኢስታንቡል ውስጥ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 3ኛው የቱርክ - የአፍሪካ ትብብር ጉባኤ ተጠናቋል።

ጉባዔው ስልታዊና ዘላቂ ግንኙነቶች መሠረት የሚጥል ነው ተብሏል።

ጉባዔው ላይ ፦
- 16 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣
- 102 ሚኒስትሮች፣
- 26 ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ተሳትፈውበታል።

በስብሰባው ላይ ሲሳተፉ የነበሩት የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሉዑካን ቡድናቸው ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

@tikvahethiopia
#Update

ሶማሊ ክልል በሚገኙ 78 ወረዳዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሁለት ወራት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከ146 ሺ በላይ ከብት፣ ግመልና ፍየሎች መሞታቸውን የሶማሊ ክልል አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ አስታውቋል።

በክልሉ ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና በሲቲ ዞን ውስጥ በሚገኙ 5 ወረዳዎች ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ወደ 3.4 ሚሊዮን ከፍ እንዳለ ቢሮው መግለፁን ሪፖርተር ዘግቧል።

በክልሉ ውስጥ ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ ዘጠኙ ዝናብ ያገኙ የነበሩት ከቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል በተለይ በመኸርና በበልግ ወራት ነው፡፡

ይሁንና በ2013 ዓ/ም ከሚያዝያ- ሰኔ የቆየው የበልግ ወቅት የዘነበው ዝናብ ዝቅተኛ በመሆኑና አሁን እየተጠናቀቀ ባለው የመኸር ወቅት ሙሉ በሙሉ ባለመዝነቡ በክልሉ ውስጥ የተከሰተው ድርቅ 6 ወራት ሆኖታል፡፡

እነዚህ ዞኖች እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓውያን ወር ድረስ ማግኘት የነበረባቸውን ዝናብ ባለማግኘታቸውና ደረቅ የሆነው የበጋ ወቅት እየገባ በመሆኑ ድርቁ ይቀጥላል የሚል ሥጋት እንዳለ ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክንያት አሁን በተከሰተው ድርቅ 3.4 ሚሊዮን የደረሰው የዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር በትንሹ አራት ሚሊዮን ይደርሳል የሚል ግምት ተቀምጧል።

አሁን ላይ ያለው ድርቅ በተለይ በዳዋ፣አፋሌር፣ ሸበሌና ኮራይ ዞኖች ተፅዕኖው እንደከፋ የተገለጸ ሲሆን ድርቁን መቋቋም ያቃታቸውና አቅም ያላቸው ነዋሪዎች እንስሳቶቻቸውን በመኪና እየጫኑ ከ600 ኪ.ሜ በላይ በመጓዝ ወደ ጅግጅጋ አቅራቢያ መምጣታቸው ታውቋል፡፡

ይሁንና እንስሳቶቻቸው በድርቁ እጅጉን በመጎዳታቸው በጉዞ ላይ እያሉና ከመኪና ሲወርዱ ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል: telegra.ph/RE-12-19

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአፋር ክልል ለ #ኦፕቲካል_ፋይበር_ጥገና ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ኃይል ይቋረጣል።

የኮምቦልቻ - ሠመራ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ትናንት ተጠናቋል።

ነገግ ግን የኦፕቲካል ፋይበር ጥገና ባለመጠናቀቁ በአፋር ክልል ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ኃይል እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።

ኃይል ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች ትናንት የተጠናቀቁ ቢሆንም የኦፕቲካል ፋይበር ጥገና ቀሪ ስራዎችን ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በመስራት ሙሉ በሙሉ ጥገናውን ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የኦፕቲካል ፋይበር ጥገናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ለግማሽ ቀን የሚካሄድ ይሆናል።

ሥራዎቹ እንደተጠናቀቁ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመነጋገር የአፋር ከተሞች ኃይል የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።

@tikvahethiopia
“ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባት አስደሳች ነው " - ዲያን ካስተሊክ

የሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም፣ ቮዳፎን፣ ሱሚቶሞ እና ሲዲሲ ጥምረት ልዑካንና የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አመራሮቻችን ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ኢንጂነር ባልቻ ጋር ተወያይተዋል።

ከጥምረቱ አባላት አንዱ የሆነው የቮዳኮም ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲያን ካስተሊክ፣ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ እስካሁን ላደረገው ያልተቋረጠ ድጋፍ እና መልካም ግንኙነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሚስተር ዲያን ፥ “ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባት አስደሳች ነው፡፡ እንደ ቮዳኮም ሌሎች አገራት ያለንን ልምድ ማካፈል መቻላችንም ያስደስተናል፡፡ ቮዳኮም ለዲጂታል አካታችነት እና ለፋይናንስ አገልግሎቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ በኢትዮጵያ ከቴሌኮም አቅርቦት በተጨማሪ ሌሎች እገዛዎችን ለማድረግ እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

ኢ/ር ባልቻ ሬባ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ወደ አገር ውስጥ ለሥራ የሚያስፈልጉትን ቁሳቁስ በማስገባትና የባለድርሻ አካላት ግንኙነትን በማመቻቸት ሳፋሪኮም ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት ማቅረብ እንዲችል እገዛ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

የሳፋሪኮም የውጪ ጉዳዮች እና ሬጉላቶሪ ኃላፊ ማቲው ሃርቬ-ሃሪሰን፣ ድርጅታችን የፈቃድ ግዴታዎችን እና መመሪያዎችን በመከተል በተቻለው ፍጥነት የኔትዎርክ አቅርቦቱን ለማቀላጠፍ አፅንዖት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ሚስተር ማቲው የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በጉምሩክ እና ኢምፖርት ሂደቶች ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ውይይቱ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሚገኝበትን የዝግጅት ደረጃ እና በቀጣይ የሚሠሩ ሥራዎችን በመግለጽ ተጠናቋል፡፡

#ሳፋሪኮምኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
' 07 ' 👉 የስልክ ቁጥር መለያ - #SafaricomETH

ቢዝነስ ዴይሊ ጋዜጣ ፥ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚጀምረው የሞባይል ስልክ አገልግሎት የስልክ ቁጥሮች መለያ ቁጥር 07 እንደሚሆን ማስታወቁን ዘግቧል።

እንደጋዜጣው ዘገባ ሳፋሪኮም በኬንያ ለሚሰጠው የሞባይል አገልግሎት የሚጠቀመው መለያ ቁጥር 07 ሲሆን አሁን ኢትዮ ቴሌኮም ከሚጠቀምበት መለያ ቁጥር 09. ቀጥሎ በሀገሪቱ ሁለተኛው ይሆናል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን እየቀጠረ ሲሆን ጥር ወር ላይ ብቻ 100 ሠራተኞችን እንደሚቀጥር አሳውቋል።

ምንጭ፦ https://www.businessdailyafrica.com/bd/corporate/companies/safaricom-set-use-07-prefix-ethiopia-phones-3655590

@tikvahethiopia
#MarakiEngraving

🎄ዘመን ተሻጋሪ ጊዜ ማይሽረው ልዩ ስጦታ🎄
🎁ከእንጨት የተሠራ Postcard
☎️0953144144 / 0915089555
📌አድራሻ- መገናኛ ገነት ኮሜርሻል 4ኛ ፎቅ 412
👇join our channel
https://publielectoral.lat/maraki_engraving
#Fagta

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰብል ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ።

በአዊ ብ/አስተዳደር በፋግታ ለኮማ ወረዳ በጋፈራ እና በዘበላ ግራይታ ቀበሌ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በመከር ሰብልና በመስኖ ሰብል ከባድ ጉዳት ማድረሱን ተጎጂ አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ጉዳት ከደረሰባቸው የመኸር ሰብሎች መካከል ጤፍ ፣ ስንዴ፣ አተር እና ገብስ እንዲሁም በመስኖ ድንች፣ የጓሮ አትክል ይገኙበታል።

የፋግታ ኮሙዩኒኬሽን ፥ የጉዳት መጠኑን በተመለከተ ተጣርቶ በቀጣይ እንደሚገልፅ አሳውቋል።

@tikvahethiopia